06
Mar
ዘጠኝ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በ8ኛው የሁዋዌ ክፍለ አህጉራዊ የአይሲቲ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር ቱኒዚያ ገብተዋል፡፡ በየዓመቱ የሚካሄደው የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ8ኛ ጊዜና በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተካሄ ይገኛል፡፡ የአገር አቀፍ ማጣሪያና ማጠቃለያ ውድድር ከተካሄደ በኋላ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አገራቸውን ወክለው በቱኒዚያ በሚካሄደው 8ኛው የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር 2023-2024 ክፈለ አህጉራዊ የፍፃሜ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ቱኒዚያ ይገኛሉ። በውድድሩ ከዘጠኝ አገሮች ከተውጣጡ 90 ተማሪዎች ጋር የሚወዳደሩ ሲሆን እነዚህም አገራት ኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ ናቸው። ለዚህ አመት ውድድር ከ1,000 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን 280 ተማሪዎች ካሉበት ሆነው…