03
Dec
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስፈላጊዉን መስፈርት አሟልተዋል ያላቸዉን 10 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን እንዲያድጉ መወሰኑ ተገልጿል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበኩሉ እንዳስታወቀው በስሩ ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መካከል 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸውን አሳዉቋል። አሁን በስራ ላይ ካሉ 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያደጉት አዳማ ባህርዳር ፣ ቦሌ ለሚ ፣ ደብረ ብረሃን እና ሀዋሳ ፣ ጅማ ፣ ቂሊንጦ ፣ ኮምቦልቻ ፣ መቀሌ እና ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መሆናቸው ታዉቋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለማሳደግ አዋጅ ቁጥር 1322/2016 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል። ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ…