Illegalmigration

ፖሊስ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ ያዘዋወሩ ተጠርጣሪዎች መያዙን ገለጸ

ፖሊስ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ ያዘዋወሩ ተጠርጣሪዎች መያዙን ገለጸ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " ከ60 በላይ ስደተኞች ለሞት እና በርካታ ሴቶች ለመደፈር ተጠያቂ ናቸው " ያላቸውን 17 አደገኛ ተጠርጣሪ የሰዎች አዘዋዋሪዎች መያዙን አስታውቋል። ፖሊስ እንደገለጸው፣ በ"መሐመድ ጣሂር አደም (ወርዲ)" የሚመራው ቡድን ሰዎችን ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በደላሎች አማካኝነት በመልመል በጂቡቲና በየመን በኩል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያዘዋውር ነበር። እነዚህ አዘዋዋሪዎች ከ40 ሺህ በላይ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ እንዳዘዋወሩ እና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ እንደሰበሰቡ ተገልጿል። ተጎጂዎች በየመን ውስጥ በመጋዘኖች ታግተው ድብደባ፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደተፈጸሙባቸው ሲገለጽ፣ ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ እንዲልኩ ለማስገደድ የስቃይ ቪዲዮዎች ይላኩ እንደነበር ተጠቁሟል። በምርመራውም ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸውና በርካታ ሴቶች መደፈራቸው መረጋገጡን ፖሊስ በመግለጫው ላይ…
Read More
በህገወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ዱባይ ሲልክ የነበረው ሰው በ20 ዓመት እስራት ተቀጣ

በህገወጥ መንገድ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ዱባይ ሲልክ የነበረው ሰው በ20 ዓመት እስራት ተቀጣ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ  ቢቂላ ከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆነው ግለሠብ ከሚመለከተው አካል እውቅና ፈቃድ ሣያገኝ ሰዎችን ወደ ዱባይ የሚልከው ግለሠብ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታዉቋል። የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሐላፊ ዋና ኢንስፔክተር ከድር ጅቦ እንደተናገሩት ተከሣሽ ገመቹ  ሰይድ የተባለው ግለሠብ ከሚመለከተው አካል እውቅና ፈቃድ ሣይኖረው  በዶዶላ ወረዳ ቢቂላ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ግለሠቦችን ከፍተኛ የስራ ልምድና ችሎታ  ስላላችሁ ስራ የማግኘት እድላችሁ ሰፊ ነው በማለት የማታለያ ቃል በመጠቀም ወደ ዱባይ እንደላካቸው ገልፀዋል። ተከሣሹ የተለያዩ  አሣማኝና  ማታለያ ቃላቶችን በመጠቀም ከሁለቱ ግለሠቦች 250 ብር በአጠቃላይ 500 ሺህ ብር በመቀበል ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬት ዱባይ ከተማ የላካቸው መሆኑ…
Read More