smuggler

ፖሊስ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ ያዘዋወሩ ተጠርጣሪዎች መያዙን ገለጸ

ፖሊስ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ ያዘዋወሩ ተጠርጣሪዎች መያዙን ገለጸ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " ከ60 በላይ ስደተኞች ለሞት እና በርካታ ሴቶች ለመደፈር ተጠያቂ ናቸው " ያላቸውን 17 አደገኛ ተጠርጣሪ የሰዎች አዘዋዋሪዎች መያዙን አስታውቋል። ፖሊስ እንደገለጸው፣ በ"መሐመድ ጣሂር አደም (ወርዲ)" የሚመራው ቡድን ሰዎችን ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በደላሎች አማካኝነት በመልመል በጂቡቲና በየመን በኩል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያዘዋውር ነበር። እነዚህ አዘዋዋሪዎች ከ40 ሺህ በላይ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ እንዳዘዋወሩ እና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ እንደሰበሰቡ ተገልጿል። ተጎጂዎች በየመን ውስጥ በመጋዘኖች ታግተው ድብደባ፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደተፈጸሙባቸው ሲገለጽ፣ ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ እንዲልኩ ለማስገደድ የስቃይ ቪዲዮዎች ይላኩ እንደነበር ተጠቁሟል። በምርመራውም ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸውና በርካታ ሴቶች መደፈራቸው መረጋገጡን ፖሊስ በመግለጫው ላይ…
Read More
ኢትዮጵያ 59 ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በእስራት ቀጣች

ኢትዮጵያ 59 ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በእስራት ቀጣች

ኢትዮጵያ 59 ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በእስራት ቀጣች በኦሮሚያ ክልል በህገወጥ የሰዎች  ዝውውር እና ድንበር በማሻገር የተከሰሱ 161 ደላሎች መካከል 59 ያህሉ ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል፡፡ የኦሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ ቢሮ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ቁጥጥር  ቡድን መሪ አቶ መሀመድ ዝያድ  እንዳሉት ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በእስራት ተቀጥተዋል፡፡ የህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ድንበር የማሻገር ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩት ግለሰቦች ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ታንዛኒያ እና ሊቢያ ጠረፎች ካሉ ደላሎች ጋር በቅንጅት ሲሰሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሰለባ የሆኑ 134 ግለሰቦች በህገወጥ መንገድ ከሀገር በመዉጣታቸዉ ለተለያዩ ጥቃቶች መዳረጋቸዉን ገልጸዋል። በነዚህ ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ምክንያት ሰለባ ከሖኑት ከ134 ግለሰቦች መካከል  112ቱ  የሚሆኑት…
Read More