FederalPolice

ፖሊስ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ ያዘዋወሩ ተጠርጣሪዎች መያዙን ገለጸ

ፖሊስ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ ያዘዋወሩ ተጠርጣሪዎች መያዙን ገለጸ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ " ከ60 በላይ ስደተኞች ለሞት እና በርካታ ሴቶች ለመደፈር ተጠያቂ ናቸው " ያላቸውን 17 አደገኛ ተጠርጣሪ የሰዎች አዘዋዋሪዎች መያዙን አስታውቋል። ፖሊስ እንደገለጸው፣ በ"መሐመድ ጣሂር አደም (ወርዲ)" የሚመራው ቡድን ሰዎችን ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በደላሎች አማካኝነት በመልመል በጂቡቲና በየመን በኩል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያዘዋውር ነበር። እነዚህ አዘዋዋሪዎች ከ40 ሺህ በላይ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ እንዳዘዋወሩ እና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ እንደሰበሰቡ ተገልጿል። ተጎጂዎች በየመን ውስጥ በመጋዘኖች ታግተው ድብደባ፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደተፈጸሙባቸው ሲገለጽ፣ ቤተሰቦቻቸውን ገንዘብ እንዲልኩ ለማስገደድ የስቃይ ቪዲዮዎች ይላኩ እንደነበር ተጠቁሟል። በምርመራውም ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸውና በርካታ ሴቶች መደፈራቸው መረጋገጡን ፖሊስ በመግለጫው ላይ…
Read More
አረብ ኢምሬት የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለኢትዮጵያ አሳልፋ ሰጠች

አረብ ኢምሬት የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለኢትዮጵያ አሳልፋ ሰጠች

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ እና ደስታ ተገኝ የተባሉ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም 105 ዜጎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዱባይ በመውሰድና ከ188 ሚሊየን ብር በላይ ከተጎጂዎች በመሰብሰብ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ የቆዩ በመሆናቸው ከዱባይ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ሥር ውለው ለኢትዮጵያ ተላልፈው እንዲሰጡ ተደርጓል ብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ዱባይ ተቀምጠው ሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው አማካኝነት ወጣቶችን በመመልመል ወደ ዱባይ በመላክ፣ በተዘጋጀ የማገቻ ቦታ በማቆየት፣ በተለይ በሴቶች ላይ ጥቃት በማድረስና በማሰቃየት ከፍተኛ ወንጀል ሲፈጽሙ የቆዩ መሆናቸው ተረጋግጧል። ፌደራል ፖሊስም ጉዳዩን ሲያጣራ ቆይቶ…
Read More
ፖሊስ ከሶስት ባንኮች 89 ሚሊዮን ብር ያጭበረበረውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ

ፖሊስ ከሶስት ባንኮች 89 ሚሊዮን ብር ያጭበረበረውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ

በሶስት ባንኮች ላይ የ89 ሚሊዮን ብር ምዝበራ የፈጸመው ቡድን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በሐሰተኛ የባንክ ዋስትና ሰነድ በመጠቀም በገዳ ባንክ፣ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ በተቀነባበረ ሴራ በአጠቃላይ ከ89 ሚሊዮን 296 ሺህ ብር በላይ በሀገር ኢኮኖሚ እና በባንኮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብሏል። ተጠርጣሪው የጎደር ዋይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ጌታሁን መለስ ሲሆን፣ ከገዳ ባንክ አገምሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አብዲሳ ቶሎሳ ጋር በጥቅም በመመሳጠር የቅርንጫፉን ፊርማና ማህተም ለወንጀል ተግባራቸው ሲጠቀሙበት መቆየታቸው ተገልጿል። ዋነኛው ተጠርጣሪ…
Read More
ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች

ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች

ኢትዮጵያ በወንጀል የምትፈልጋቸውን ሰዎች አሜሪካ አሳልፋ እንድትሰጣት ጥያቄ አቅርባለች፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአሜሪካው ኤፍ.ቢ.አይ (FBI) ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አምባሳደሩ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ኮሚሽነሩ በውይያታቸው ወቅት ጠይቀዋል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ በተለይም በአሜሪካን ሀገር እየኖሩ የሀገሪቱን ሰላም እያወኩ ነው በሚል የምትጠረጥራቸውን ሰዎች ተላልፈው እንዲሰጧት ለአምባሳደሩ ጥያቄ እንዳቀረቡም ተገልጿል፡፡ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በአሜሪካን መንግሥት የሚፈለጉ ወንጀለኞችን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አሳልፎ በመስጠት ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ተብሏል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተመሳሳይ ድጋፎችን እንድታደርግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ…
Read More