31
Jul
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2016 በጀት አመት ሃብታቸውን ካስመዘገቡት አመራሮች መካከል በተጨማሪም የሃብት ማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በአንድ መቶ አስራ ሦስት ውሳኔ ሰጪ አመራሮች ላይ የሃብት ማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን የኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን በላይነህ ተናረዋል፡፡ ያስመዘገቡት ሃብት አጠራጣሪ ሁኖ በተገኙና በተደረጉ ጥቆማዎች መሰረት በውሳኔ ሰጪ አመራሮች ላይ የሃብት ማጣራት ሥራ እየተሰራ እንዳለ ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡ ኮሚሽኑ በሚሰራው የሃብት ማጣራት ሥራ ሃታቸው ለሙስና የተጋለጡትን ለፍትህ ሚኒስቴር እንደሚሳውቅም ጠቁመዋል፡፡ ሃብታቸው እየተጣራ ያሉትን ውሳኔ ሰጪ አመራሮች በአሁኑ ሰዓት ይፋ ማድርጉ ያልተመዘገቡ ሃብቶችን እንዲያሸሹ ስለሚያደርግ ከማጣራት ሥራው በኋላ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ ከህብረተሰቡ ጋር በይበልጥ…