Hawasa

ሲዳማ ክልል እንዲሆን ብዙ ዋጋ ብንከፍልም የጠበቅነውን ለውጥ ማየት አልቻልንም ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

ሲዳማ ክልል እንዲሆን ብዙ ዋጋ ብንከፍልም የጠበቅነውን ለውጥ ማየት አልቻልንም ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

የክልሉ መንግስት ግን በዓመት ከ60 ሺህ በላይ የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ክልል እንሁን ከሚል ወደ ልማት ጥያቄ ዞሯል ብለዋል በቀድሞው የደቡብ ክልል ስር ከነበሩ ዞኖች መካከል አንዱ የነበረው የሲዳማ ዞን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ 11ኛው የኢትዮጵያ ክልል ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በአራት ዞኖች እና አንድ ከተማ አስተዳድር የተዋቀረው ሲዳማ ክልል ከህዝበ ውሳኔ በኋላ ህይወት እንዴት እየቀጠለ እንደሆነ ኢትዮ ነጋሪ የክልሉን ነዋሪዎች አነጋግራለች፡፡ ለደህንነቱ በመስጋት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ እንዳለን ከሆነ “ሲዳማ ክልል እንዲሆን ቤተሰቤን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች ዋጋ ከፍለናል፡፡ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው እየተጠቀሙ ያሉት፣ ስራ ማግኘት አልቻልንም” ሲል ተናግሯል፡፡ “ሲዳማ…
Read More
ፓስተር ዮናታን የ77 ሚሊዮን ብር የባንክ እዳ እንዳለባቸው ተገለጸ

ፓስተር ዮናታን የ77 ሚሊዮን ብር የባንክ እዳ እንዳለባቸው ተገለጸ

በፓስተር ዮናታን ንብረቶች ላይ ንብ ባንክ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አወጣ። ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ላበደረው ንብረት የሐራጅ ሽያጭ አውጥቷል። ንብ ባንክ በሰኔ 22 ቀን የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባስወጣው የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ መሰረት በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ባሉ የመኖሪያ ቤት እና ንግድ ድርጅቶችን ለመሸጥ ለተጫራጮች ማስታወቂያ አውጥቷል። አበዳሪው ወይም የመያዢያ ሰጪ ስም፣ አበዳሪው ቅርንጫፍ፣ የሚሸጠው ንብረት ዓይነትና የሚገኝበት ቦታ፣ የሐራጁ መነሻ በብር፣ የሐራጁ ቀንና ሰዓትም ተገልጿል። ጨረታ ከወጣባቸው ንብረቶች መካለም አቶ ዮናታን አኪሊሉ አንጀሎ አራት ኪሎ ፕሪሚየም፣ በስማቸው የተመዘገበ ሀዋሳ ምሥራቅ ከተማ የሚገኝ 400 ሜትር ካሬ ቦታ ያለው ባለ 3 ወለል መኖሪያ ቤት ሲሆን የሐራጁ መነሻ ዋጋ 22 ሚሊዮን ብር…
Read More