goodgovernance

ሲዳማ ክልል እንዲሆን ብዙ ዋጋ ብንከፍልም የጠበቅነውን ለውጥ ማየት አልቻልንም ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

ሲዳማ ክልል እንዲሆን ብዙ ዋጋ ብንከፍልም የጠበቅነውን ለውጥ ማየት አልቻልንም ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

የክልሉ መንግስት ግን በዓመት ከ60 ሺህ በላይ የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ክልል እንሁን ከሚል ወደ ልማት ጥያቄ ዞሯል ብለዋል በቀድሞው የደቡብ ክልል ስር ከነበሩ ዞኖች መካከል አንዱ የነበረው የሲዳማ ዞን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ 11ኛው የኢትዮጵያ ክልል ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በአራት ዞኖች እና አንድ ከተማ አስተዳድር የተዋቀረው ሲዳማ ክልል ከህዝበ ውሳኔ በኋላ ህይወት እንዴት እየቀጠለ እንደሆነ ኢትዮ ነጋሪ የክልሉን ነዋሪዎች አነጋግራለች፡፡ ለደህንነቱ በመስጋት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ እንዳለን ከሆነ “ሲዳማ ክልል እንዲሆን ቤተሰቤን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች ዋጋ ከፍለናል፡፡ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው እየተጠቀሙ ያሉት፣ ስራ ማግኘት አልቻልንም” ሲል ተናግሯል፡፡ “ሲዳማ…
Read More