Sidama

ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ሀይሉን ባልሆነ ቦታ እያባከነ ይሆን?

ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ሀይሉን ባልሆነ ቦታ እያባከነ ይሆን?

የኢትዮጵያ ሐገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሁሉን አቀፍ የሆነ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግና ከዚህ በፊት ይነሱ  የነበሩ ትርክቶች መቋጫ እንዲያገኙ በሚል ነበር በ2014 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቋቁሞ ስራ የጀመረው፡፡ በዚህም ባለፉት ሶስት ዓመታት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብቶ የአጀንዳ መለየትና ሌሎች እንቅስቃሴዎችንም በመስራት ላይ ይገኛል። ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት አዲስ አበባን ጨምሮ በሲዳማ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋር፣ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ደቡብ ምዕራብ ፣ ኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች አጀንዳዎችን መለየቱን አስታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎ ኢትዮ ነጋሪ የሲዳማ ክልል የሕብረተሰብ ክፍሎች በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ ያላቸውን ዕምነት እና በኮሚሽኑ በአጀንዳነት እንዲካተት ስለሚፈልጓቸው ጉዳዮች ዙሪያ ቃለ መጠይቅ አድርጓል፡፡ የ19 ዓመቷ ተማሪ ምህረት ከበደ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ሐገራዊ ምክክር ኮሚሽን…
Read More
ሲዳማ ክልል እንዲሆን ብዙ ዋጋ ብንከፍልም የጠበቅነውን ለውጥ ማየት አልቻልንም ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

ሲዳማ ክልል እንዲሆን ብዙ ዋጋ ብንከፍልም የጠበቅነውን ለውጥ ማየት አልቻልንም ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

የክልሉ መንግስት ግን በዓመት ከ60 ሺህ በላይ የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ክልል እንሁን ከሚል ወደ ልማት ጥያቄ ዞሯል ብለዋል በቀድሞው የደቡብ ክልል ስር ከነበሩ ዞኖች መካከል አንዱ የነበረው የሲዳማ ዞን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ 11ኛው የኢትዮጵያ ክልል ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በአራት ዞኖች እና አንድ ከተማ አስተዳድር የተዋቀረው ሲዳማ ክልል ከህዝበ ውሳኔ በኋላ ህይወት እንዴት እየቀጠለ እንደሆነ ኢትዮ ነጋሪ የክልሉን ነዋሪዎች አነጋግራለች፡፡ ለደህንነቱ በመስጋት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ እንዳለን ከሆነ “ሲዳማ ክልል እንዲሆን ቤተሰቤን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች ዋጋ ከፍለናል፡፡ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው እየተጠቀሙ ያሉት፣ ስራ ማግኘት አልቻልንም” ሲል ተናግሯል፡፡ “ሲዳማ…
Read More
ሐዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ክልል ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ምን ላይ ናቸው?

ሐዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ክልል ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ምን ላይ ናቸው?

ጾታዊ ጥቃት በሰዎች ላይ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ችግሮችን የሚያስከትልና ጾታን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም የኃይል ድርጊት ነው፡፡ ፍቅርተ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ስትሆን በምትኖርበት ከተማ ውስጥ የጾታዊ ጥቃት ምን እንደሚመስል ለጠየቅናት ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥታናለች፡፡ “ጾታዊ ጥቃት በቅርብ ሰው፣ በምናውቀው ሰው ነው የሚፈጸመው፡፡ በከተማዋ እና አቅራቢያ ብዙ አይነት ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳሉ ይሰማኛል” ብላለች፡፡ “ወደ አደባባይ ያልወጡ ብዙ የጾታ ጥቃት ወንጀሎች አሉ” የምትለው ፍቅርተ “በቅርቡ የ14 ዓመት ጓደኛዬ በአጎቷ ተደፍራለች፡፡ እናት እና አባቷ ለማህበራዊ ጉዳይ ከቤታቸው ሲሄዱ አጎቷ ጋር እንድትሆን ብለው በአደራ አስቀመጧት፡፡ ነገር ግን የተሻለ ደህንነት አለው ብለው ባስቀመጧት ቤት ያስቀመጧት ይህች የ14 ዓመት ታዳጊ አጎቷ አስገድዶ ደፍሯታል፡፡…
Read More
ሙሽራዋ በሰርጓ ዕለት የባሏን ሞት ተረዳች

ሙሽራዋ በሰርጓ ዕለት የባሏን ሞት ተረዳች

በሀዋሳ አቅራቢያ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ ሙሽራውን ጨምሮ 74 ሰዎች ሞተዋል። በትናንትናው ዕለት በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ልዩ ስሙ ጋላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ ሙሽራውን ጨምሮ የ74 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ማቴ መንገሻ (ዶ/ር) እንዳሉት "አይሱዚው 11 ሰዓት አካባቢ መነሻዉን ቦና ወረዳ ሚሪዴ ገጠር ቀበሌ አድርጎ ወራንቻ ወደተባለ አጎራበች ቀበሌ የወንድ ወገን የሆኑ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ሴቷ ቤት ጉዞ ላይ ነበር " ብለዋል። ገላና ድልድይ ላይ ሲደርስ ግን ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ እስካሁን በተጣራዉ በአጠቃላይ የ74 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል። በ4 ሰዎች ላይ ከፍተኛ…
Read More