30
Dec
በሀዋሳ አቅራቢያ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ ሙሽራውን ጨምሮ 74 ሰዎች ሞተዋል። በትናንትናው ዕለት በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ልዩ ስሙ ጋላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ ሙሽራውን ጨምሮ የ74 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ማቴ መንገሻ (ዶ/ር) እንዳሉት "አይሱዚው 11 ሰዓት አካባቢ መነሻዉን ቦና ወረዳ ሚሪዴ ገጠር ቀበሌ አድርጎ ወራንቻ ወደተባለ አጎራበች ቀበሌ የወንድ ወገን የሆኑ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ሴቷ ቤት ጉዞ ላይ ነበር " ብለዋል። ገላና ድልድይ ላይ ሲደርስ ግን ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ እስካሁን በተጣራዉ በአጠቃላይ የ74 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል። በ4 ሰዎች ላይ ከፍተኛ…