06
Jan
ጾታዊ ጥቃት በሰዎች ላይ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ችግሮችን የሚያስከትልና ጾታን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም የኃይል ድርጊት ነው፡፡ ፍቅርተ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ስትሆን በምትኖርበት ከተማ ውስጥ የጾታዊ ጥቃት ምን እንደሚመስል ለጠየቅናት ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥታናለች፡፡ “ጾታዊ ጥቃት በቅርብ ሰው፣ በምናውቀው ሰው ነው የሚፈጸመው፡፡ በከተማዋ እና አቅራቢያ ብዙ አይነት ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳሉ ይሰማኛል” ብላለች፡፡ “ወደ አደባባይ ያልወጡ ብዙ የጾታ ጥቃት ወንጀሎች አሉ” የምትለው ፍቅርተ “በቅርቡ የ14 ዓመት ጓደኛዬ በአጎቷ ተደፍራለች፡፡ እናት እና አባቷ ለማህበራዊ ጉዳይ ከቤታቸው ሲሄዱ አጎቷ ጋር እንድትሆን ብለው በአደራ አስቀመጧት፡፡ ነገር ግን የተሻለ ደህንነት አለው ብለው ባስቀመጧት ቤት ያስቀመጧት ይህች የ14 ዓመት ታዳጊ አጎቷ አስገድዶ ደፍሯታል፡፡…