21
Feb
ኢትዮጵያ አራት አይነት ፓስፖርቶችን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጋለች የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ፓስፖርቶችን ይፋ አድርጓል። ዛሬ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ይፋ የተደረጉት ፓስፖርቶች አራት አይነት ሲሆኑ ከመደበኛ ፓስፖርት በተጨማሪ የዲፕሎማት፣ ውጭ ሀገራት እና የአገልግሎት ፓስፖርቶችም ይገኙበታል። ፓስፖርቶቹ በጃፓኑ ቶፓን የደህንነት ኩባንያ እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ኩባንያ ትብብር ስለመመረቱም ተገልጿል። 10 ዓመት እንዲያገለግል ተደርጎ የተሰራው ይህ ፓስፖርት በአዲስ አበባ በሚገኘው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተመረተ ነው። የፓስፖርቱ አገልግሎት ጊዜ 10 ዓመት መደረግ የዜጎችን ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት እንደሚቆጥብ ተገልጿል። ይህ በዚህ እንዳለም በፓስፖርቱ ውስጥ ገጾች ላይ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታዎች የሚያጎለብቱ እና ታሪካዊ ቅርጾችን ይዟልም ተብሏል። እንዲሁም ፓስፖርቱ የማይክሮ ችፕስ የተገጠመለት…