Visa

ኢትዮጵያ ከ14 ሺህ በላይ የውጭ ሀገራት ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ሰጠች

ኢትዮጵያ ከ14 ሺህ በላይ የውጭ ሀገራት ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ሰጠች

ሀገሪቱ ለ20 የውጭ ዜግነት ለነበራቸው ሰዎች የኢትዮጵየዊ ዜግነት ሰጥታለች ተብሏል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተቋሙን የስድስት ወራት አፈጻጸም አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው ላይ እንዳሉት ለ14 ሺህ 367 ለሚሆኑ የውጭ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለ20 ግለሰቦች ደግሞ የኢትዮጵያዊ ዜግነት እንደተሰጣቸውም ወይዘሮ ሰላማዊት በመግለጫው ለይ ጠቅሰዋል። ተቋሙ ለዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሠው ሀይሉን የማጠናከር፤ አሰራሩን በቴክኖሎጂ የማገዝ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ለጉብኝት ቱሪስት፣ ለኮንፍረንስና ለቢዝነስ የሚገቡትን ለማስተናገድ በ188 ሀገራት ቪዛ ኦን አራይቫል በመክፈት እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአየር ትራንስፖርት ወደ ኢትዮጵያ…
Read More
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ እንዲያነሳ ተጠየቀ

አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ እንዲያነሳ ተጠየቀ

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ የመስጠት ሂደት ላይ ጊዜያዊ ገደቦች ማስቀመጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ህብረቱ ውሳነውን ያሳለፈው የኢትዮጵያ መንግስት በአውሮፓ ህጋዊ መኖሪያ ያላገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተባባሪ አልሆነም በሚል የቪዛ ገደብ ጥያለሁ ብሏል፡፡ በህብረቱ አዲስ ውሳኔ መሰረትም ኢትዮጵያዊያን ከዚህ በፊት ወደ አውሮፓ ሀገራት በ15 ቀናት ውስጥ ለቪዛ ጥያቄቸው ምላሽ ያገኙ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ውሳኔ መሰረት ይህንን ወደ 45 ቀናት ከፍ አድርጓል፡፡ ውሳኔው የአገልግሎት እና ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ የቪዛ አመልካች ኢትዮጵያዊያንንም እንደሚጨምር በወቅቱ ተገልጾ ነበር፡፡ በአውሮፓ ህብረት ዋና ከተማ ብራስልስ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የአውሮፓ ህብረት ውሳኔ የሚያበሳጭ ነው ብሏል፡፡ ኢምባሲው በመግለጫው…
Read More
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያዊያን በሚሰጠው ቪዛ ዙሪያ አዲስ ገደብ ጣለ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያዊያን በሚሰጠው ቪዛ ዙሪያ አዲስ ገደብ ጣለ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያዊያን የቪዛ መጠየቂያ ጊዜን ከ15 ቀናት ወደ 45 ቀናት ከፍ አድርጓል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ የመስጠትን ሂደት ላይ ጊዜያው ገደቦችን ማስቀመጡን አስታውቋል። ህብረቱ በሳለፈው ውሳኔ የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ ሊያሟሉ ይገባቸዋል ያላቸውን መስፈርቶችም አስቀምጧል። በዚህም ኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ሀገራት ቪዛን ለማግኘት አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ ይገደዳሉ ተብሏል። በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት አይችሉም ሲልም ከልክሏል። ለዲፕሎማቲክ እና ለአገልግሎት ፓስፖርቶች የቪዛ ክፍያን በተመለከተም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛውን የቪዛ ክፍያ ለመክፈል ይገደዳሉ ብሏል ህብረቱ።…
Read More
ኢትዮጵያ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች መመዝገቢያ ጊዜን አራዘመች

ኢትዮጵያ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች መመዝገቢያ ጊዜን አራዘመች

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣው መግለጫ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅመው ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ደርሼበታለሁ ብሎ ነበር፡፡ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ፓስፖርት፣ ሀሰተኛ ቪዛ እና ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየኖሩ ይገኛል ብለዋል። በተደረገው የማጣራት ስራ ከ18 ሺህ በላይ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ከ1 ሺህ 500 በላይ ሀሰተኛ ቪዛ እና ከአንድ ሺህ 800 በላይ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያን ያሰሩ ዜጎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መገኘታቸውንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። በመሆኑም ህገወጥ ሰነድ ያለቸው ዜጎች ከጥር እስከ ጥር 30 ቀን 2016…
Read More
በኢትዮጵያ ከ20 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በሐሰተኛ ሰነዶች እንደሚኖሩ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከ20 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በሐሰተኛ ሰነዶች እንደሚኖሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት እንዳስታወቀው የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅመው ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ፓስፖርት፣ ሀሰተኛ ቪዛ እና ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየኖሩ ይገኛል ብለዋል። በተደረገው የማጣራት ስራ ከ18 ሺህ በላይ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ከ1 ሺህ 500 በላይ ሀሰተኛ ቪዛ እና ከአንድ ሺህ 800 በላይ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያን ያሰሩ ዜጎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መገኘታቸውንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። በመሆኑም ህገወጥ ሰነድ ያለቸው ዜጎች ከጥር አንድ ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም…
Read More
ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መስጠት እንደምትጀምር ገለጸች

ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መስጠት እንደምትጀምር ገለጸች

ኢትዮጵያ የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት ለውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ከሁለት ዓመት በፊት መስጠት የጀመረች ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ እና በሌሎች ምክንያቶች ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ የጎብኚዎችን ቁጥር ከፍ እንደሚያደርግ የሚገለጸው የመዳረሻ ቮዛ አገልግሎት ከመስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ኢትዮጵያ 190 ሺህ ፓስፖርት ከውጪ ሀገር በማሳተም ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቷን ገልጻለች፡፡ የኢምግሬሽን እና ዝግጅት አገልግሎት ከሙስና ጋር በተያያዘ ሁሉንም ከፍተኛ አመራሮች ከሀላፊነት በማንሳት አዲስ አመራር ከአንድ ወር በፊት ተሾሞለታል። ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ ተቋሙን በሀላፊነት እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተሾሙት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው 300 ሺህ ዜጎች ፓስፖርት ለማግኘት ተመዝግበው እየተጠባበቁ መሆኑን…
Read More