22
Apr
ባለፋት ዘጠኝ ወራት በህገ ወጥ መንገድ የፓስፓርት አግልግሎት ለማግኘት የሞከሩ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል ተብሏል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2018 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት ያከናወናቸውን አገልግሎት አፈፃፀም በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደተናገሩት ባለፋት ዘጠኝ ወራት 3 ሺህ 6 መቶ 38 ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ የፓስፓርት አግልግሎት ለማግኘት የተጭበረበረ ሰነድ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ነበር። ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ 300 የውጭ ዜጎች እና 3ሺህ3 መቶ 38 ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ አገልግሎት ለማግኘት የተጭበረበረ ሰነድ ይዞው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና ትክክለኛ ያልሆነ የዜግነት ማስረጃ ይዘዉ የተገኙ መሆናቸው ተጠቁሟል። በዚህም መሰረት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጋቸውን…