ከ3 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው ተገለጸ

የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እንደገለጸው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ከ3 ሺህ 400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች መያዛቸውን ጠቁሟል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የሶት ወራት ሪፖርት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

ዳይሬክተሯ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከ3 ሺህ 400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩት የውጭ ዜጎች ቪዛ ሳያገኙ ለመግባት ሲሞክሩ፣ ህገወጥ የጉዞ ሰነድ ይዞ መገኘት እና መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲሞክሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ከ1 ሺህ 500 በላይ ዜጎች ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል የተባለ ሲሆን ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በሀገር ውስጥ ቆይተው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

እነዚህ ዜጎች ከህግ ውጪ በሀገር ውስጥ በመቆየታቸው ቅጣት እንዲከፍሉ መደረጉንም ዋና ዳጠይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለም ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 10 ሺህ 900 ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በህገ-ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ እንደተያዙ ተገልጿል፡፡

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት 3 ወራት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ተከትሎ በተቋሙ ተልዕኮ ላይ ከፓርላማ ጥያቄ ቀርቦለታል።

ዳይሬክተሯ ሪፖርታቸው ላይ ባለፉት 3 ወራት ከሰጠው አገልግሎት 11 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 10.5 ቢሊዮን ብር እንደሰበሰበ ተናግረዋል።

ሪፖርቱን ተከትሎ የተቁሙን የቁጥጥር አቅምን ማደግ አድንቀው በሩብ ዓመት የተሰጠው የፓስፖርት አገልግሎትም የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሳዲቅ “ነገር ግን ተቋሙ ከተሰጠው ሃላፊነት አንጻር ወደ ገቢ መሰብሰብ አመዝኗል ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ ወደ 11 ቢሊዮን ለመሰብሰብ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ማቀዱን ያስታወሱት የምክር ቤት አባሉ የገልግሎቱ ቀዳሚ ግብ ገቢ መሰብሰብ ነው ወይስ? አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ነው ካሉ በኋላ ማብራርያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

አገልግሎቱ ገቢ ላይ ትክረቱን አድርጓል በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የምንሰጠው አገልግሎት ስለሆነ በዚህም ብዙ ገንዘብ እንደሚሰበሰብ ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ ባህሪ አገልግሎት መስጠት ነው በዚህም በተለያ የውጭ አገር ሰዎች ሲመጡ ቪዛ እንሰጣለን ይህ አገልግሎት ደግሞ በየትኛውም አለም በገንዘብ የተተመነ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በግባችን መሰረት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ እና ወደ ብሔራዊ ቋት ማስገባት ካልቻልን የተቋሙን አቅም ማሳደግ አንችልም ብለዋል ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፡፡

የተቋሙ ገቢ ባደገ ቁጥር ለራሱም የሚጠቀመው ከሚሰበስበው ስለሆነ ሁሌ የሚለምን ተቋም መሆን የለበትም ምክንያቱ ደግሞ ቴክኖሎጂው በየጊዜው ስለሚቀያየር ሲሉ እራሱን ማሻሻል እንዳለበት ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ቀደምም በመንግስት ስም አገልግሎቱ ገቢ እንደሚሰበስብ የተናገሩት ወ/ሮ ሰላማዊት እኛ ያደረግነው የቀድሞውን ወይንም የነበረውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ነው ብለዋል፡፡

ሰዎች ብዙ ጊዜ ገቢው የሚሰበሰበው ከፓስፖርት ይመስላቸዋል እሱን ግን ስህተት ነው ያሉት ዳይሬክተሯ ከገቢው ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ግን ከቪዛ እና ተያያዥ አገልግሎቶች መሆናቸውን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሯ አክለውም ላይ ባለፉት 3 ወራት ከ545,000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ፓስፖርት አግኝተዋል ብለዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *