12
Jul
በኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሰዎች ፓስፖርት ተሰጥቷል ተብሏል የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዓመታዊ አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት በ2016 አመት 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ፓስፖርት ለአመልካቾ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ በታሪኩ ይህን መጠን ያለዉ ፓስፖርት ለአገልግሎት ፈላጊዎች ሲሰጥ የመጀመሪያዉ መሆኑን ዳይሬክተሯ ጠቅሰዋል። ይህ በዚህ እንዳለም ተቋሙ ከፓስፖርት እና ሌሎች አገልግሎት ክፍያዎች 14 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንም ተናግረዋል። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ጭምር ቅሬታ ሲቀርብበት ቢሰማም እንዲሁም ተገልጋዮች አሁንም ቅሬታ ማቅረባቸዉን ቢቀጥሉም ፤ ተቋሙ አሰራሮቼን እያስተካከልኩ እገኛለሁ ብሏል። ዋና ዳይሬክተሯ ፤ ከዚህ…