24
May
ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን እና የውጪ ንግድን ለማሳደግ በሚል ነበር ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የገነባችው፡፡ አሁን ላይ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሏት ኢትዮጵያ ፓርኮች የምርታቸውን 50 በመቶ ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ፈቅዳለች፡፡ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ መፈቀዱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች ምርታቸውን ሙሉ በሙሉ ለውጭ ገበያ እንጂ ለሀገር ውስጥ ማቅረብ ሳይፈቀድላቸው መቆየቱን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን ገልጸዋል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ተጽዕኖ ሥር የነበሩ ባለሃብቶችን ለማበረታታት በፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ በአዋጅ መፈቀዱን አስታውቀዋል። ከሁለት ዓመት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ አሜሪካ…