Courtreporting

በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ጋዜጠኞች የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቆ ሆኖ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ተወሰነ

በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ጋዜጠኞች የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቆ ሆኖ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ተወሰነ

አራት የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረጓል። በሽብር ወንጀል የተከሰሱ አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ፤ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ። የተከሳሾችን በቁጥጥር ስር መዋል በተመለከተ የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣውን መግለጫ በድረ ገጻቸው የጫኑ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎቻቸውን እንዲያወርዱም ፍርድ ቤቱ አዝዟል። ይህን ትዕዛዝ የሰጠው ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ነው። ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ትዕዛዞችን በሰጠበት ቅጽበት ተከሳሾች በጭብጨባ የታጀበ መፈክር አሰምተዋል። የተከሳሾቹ መፈክር እና ጭብጨባ፤ የችሎት ውሎ…
Read More
እነ ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነጻ ተሰናበቱ

እነ ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነጻ ተሰናበቱ

ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱን ጨምሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱን ጨምሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በነጻ አሰናብቷቸዋል፡፡  ፍርድ ቤቱ ብይኑን የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 4፤ 2015 በዋለው ችሎት ነው፡፡  በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፤ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ በፍርድ ቤቱ በይኗል። ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው፤ “ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሰው…
Read More