16
Jul
የሁለቱ ሀገራት ማእከላዊ ባንኮች ገንዘባቸው አሁን ባለው የመግዛት አቅም ልክ 46 ቢሊዮን ብር እና 3 ቢሊየን ድርሀም ለመቀያየር ተስማምተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት የሚያስችላቸውን የመግባብያ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ ሀገራቱ ከአሜሪካን ዶላር ባለፈ እርስ በእርስ በሚያደርጓቸው ግብይቶች ብር እና ድርሀምን ለመጠቀም ነው የተስማሙት፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ካሊድ ሞሃመድ ባላማ ተፈራርመዋል፡፡ ሀገራቱ በቀጣይ ዝርዝር አሰራሮች እና መመሪያዎች ላይ በጥልቀት የሚወያዩ ሲሆን ግብይቱን ለማሳለጥ ገንዘባቸው አሁን ባለው የመግዛት አቅም ልክ 46 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር እና 3 ቢሊየን የዩኤኢ ድርሀም በማከላዊ ባንኮቹ በኩል ለመቀያየር ተስማምተዋል፡፡ ስምምነቱ አዲስ አበባ…