investethiopia2023

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፍሰት የሁለት ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፍሰት የሁለት ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ አቅዳ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርቱ ላይ እንደገለጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እንዳሉት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ወደ አገር ውስጥ ለመሳብ ታቅዶ 2.67 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ የኮሚሽኑ አፈጻጸም የዕቅዱን 61 በመቶ ብቻ ያሳካ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት፣ በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያለው አለመረጋጋት እንዲሁም በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ምክንያት ያጋጠመው የዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ለአፈጻጸሙ መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡ ወደ…
Read More
ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 51 ባለሀብቶች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ

ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 51 ባለሀብቶች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተሰማሩ የውጭ ሀገራት ኢንቨስተሮች በሙስና ምክንያት ከሚሰሩባቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለቀው እየወጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የበጀት ዓመቱን ዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ የምርት ዘርፎች የተሰማሩ የውጭ ሀገራት ኩባንያዎች ከመንግስት ተቋማት መሪዎች እና ባለሙያዎች በሚጠየቁ ክፍያ ምክንያት መማረራቸው ተገልጿል፡፡ ምክር ቤቱ የኢንቨስትመንት ኮሚሽኑንን ሪፖርት በገመገመበት ወቅት እንደገለጸው በኦሮሚያ ክልል ዱከም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ ያሉ ኩባንያዎች ቅሬታ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት በዚህ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባደረጉት ምልከታ ኢንቨስተሮች የሚጠይቋቸውን ከትንሽ እስከ ትልቅ አገልግሎቶች በገንዘብ እየገዙ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም በፓርኩ ላይ የባለቤትነት ስሜት ባለመኖሩ ፓርኮች ውስጥ እየገቡ ዘረፋ እየተፈጸባቸው መሆኑን የምክር…
Read More
ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ“PW ማይኒንግ” ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ“PW ማይኒንግ” ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

የከፊ ሚኒራልስ ኩባንያ አካል የሆነው ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ 'PW ማይኒንግ' ጋር የወርቅ ማዕድን ልማትና በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ የተፈረመው ከትናንት ሚያዚያ 18/2015 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ በሚገኘው፤ “ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023” ዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማትና ባለሃብቶች ፎረም ጎን ለጎን ነው። በፎረሙ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ባለሃብቶች፣ የንግድ ተዋንያን፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ሥራ ፈጣሪዎች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን፤ በመድረኩ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቶች፣ የፓናል ውይይቶች፣ የተመረጡ ኩባንያዎች ጉብኝትና አውደ ርዕይዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨትመንት ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚከናወነው ይህ ፎረም በግብርና፣ ማንፋክቸሪንግ፣ አይ.ሲ.ቲ፣ ማዕድን እና በቱሪዝም ላይ ትኩረቱን አድርጓል። በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨሰትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፣…
Read More