29
May
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወርቅ ማዕድን 363 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ያቀደች ቢሆንም የተገኘው ግን 67 በመቶው ብቻ ነው ተብሏል፡፡ ህገ ወጥ የወርቅ ግብይት ዋነኛው ችግር መሆኑን ተከትሎ በመከላከያ ኮማንድ ፖስትና በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጭምር ክትትል ቢደረግም ህገ ወጥ የወርቅ ንግድን ማስቆም እንዳልተቻለ ማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በማዕድናት ሕገ ወጥ ግብይት፣ ኮንትሮባንድና የፀጥታ ችግር ምክንያት በባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ ሦስት ቶን ብቻ እንደሆነ፣ ይህም ከዕቅዱ 50 በመቶ ብቻ መሆኑ ታውቋል፡፡ በመጋቢት ወር ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ 350 ኪሎ ግራም ሲሆን ይህም በ2014 መጋቢት ወር ከተገኘው 800 ኪሎ ግራም በእጅጉ ያነሰ ነው ተብሏል፡፡ በአገሪቱ ያሉ ወርቅ…