mininginethiopia

ኢትዮጵያ የ4 ቢሊዮን ዶላር ማዕድን ኢንቨስትመንት ተፈራረመች

ኢትዮጵያ የ4 ቢሊዮን ዶላር ማዕድን ኢንቨስትመንት ተፈራረመች

በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ የተገለጸ የብረን ማዕድን በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ጊምቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለማውጣት ስምምነት ተፈርሟል፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና ቻይናዊያን በተቋቋሙ ኩባንያዎች መካከል የብረት ማዕድን ልማት ፕሮጀክት ዛሬ ተፈራርሟል፡፡ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው የተባለው ይህ የ10 ዓመት የብረት ማዕድን ማውጣት ስምምነት የማዕድን ሚኒስቴር እና ዜድ ዋይ ቲቢ-ዲኤይኤም ስቲል ማኑፋክቸሪንግ ከተሰኘ የግል ኩባንያ ጋር ስምምነት ፈጽሟል፡፡ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ ከስምምነቱ በኋላ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የብረት ማዕድናት እንዳሏት ካወቀች ከ70 ዓመት በላይ ቢሆናትም “እስካሁን አንድም የብረት ማዕድን አለማውጣቷን” ተናግረዋል፡፡ “በወለጋ ጊምቢ ቢቂላል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ብረት እንዳለን የታወቀው በ1956 ነበር፣ ግን እንደምታውቁት እስካሁን አንድም ብረት ማዕድን…
Read More
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከኖርዌው የማዕድን ኩባንያ የ3 ሚ. ዶላር ድርሻ ገዛ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከኖርዌው የማዕድን ኩባንያ የ3 ሚ. ዶላር ድርሻ ገዛ

የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ፡፡ የፈንዱ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ በኢትዮጵያ የወርቅ ማውጣት ሥራ ላይ ከተሠማራው የኖርዌው አኮቦ የማዕድን ኩባንያ  ሦስት ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 7.4 በመቶ ድርሻ መግዛቱን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ታዬ፤ “በአኮቦ ማዕድን የምናደርገው ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መስፋፋት ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ እመርታ ነው” ብለዋል፡፡ ውሳኔው ኢትዮጵያ ከክፍለ ዘመን በኋላ ወደ ዓለም አቀፍ የአክስዮን ገበያ እንድትመለስ ያደረገና ለቀጣይ የድንበር ተሻጋሪ ኢንቨስትመንቶች በር የከፈተ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኢንቨስትመንቱ አኮቦ አዲስ ማዕድን ማውጫ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ የሚደግፍ ሲሆን፤ ይህም የድርጅቱን ወርሃዊ የወርቅ…
Read More
ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ“PW ማይኒንግ” ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ“PW ማይኒንግ” ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

የከፊ ሚኒራልስ ኩባንያ አካል የሆነው ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ 'PW ማይኒንግ' ጋር የወርቅ ማዕድን ልማትና በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ የተፈረመው ከትናንት ሚያዚያ 18/2015 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ በሚገኘው፤ “ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023” ዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማትና ባለሃብቶች ፎረም ጎን ለጎን ነው። በፎረሙ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ባለሃብቶች፣ የንግድ ተዋንያን፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ሥራ ፈጣሪዎች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን፤ በመድረኩ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቶች፣ የፓናል ውይይቶች፣ የተመረጡ ኩባንያዎች ጉብኝትና አውደ ርዕይዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨትመንት ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚከናወነው ይህ ፎረም በግብርና፣ ማንፋክቸሪንግ፣ አይ.ሲ.ቲ፣ ማዕድን እና በቱሪዝም ላይ ትኩረቱን አድርጓል። በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨሰትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፣…
Read More
ኢትዮጵያ ለሁለት የወርቅ አውጪ ኩባንያዎች ፈቀድ ሰጠች

ኢትዮጵያ ለሁለት የወርቅ አውጪ ኩባንያዎች ፈቀድ ሰጠች

ለሁለት ሀገር በቀል ኩባንያዎች የከፍተኛ ደረጃ የደለል ወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጥቷል። የማዕድን ሚኒስቴር ለሁለት ኩባንያዎች የከፍተኛ ደረጃ የደለል ወርቅ የማምረት ፈቃድ መስጠቱን ገልጿል። ፈቃድ የተሰጣቸው ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ እና ኢልኔት ቴክኖሎጂ ግሩፕ የተሰኙት ሀገር በቀል ኩባንያዎች ናቸው። "ቤአኤካ" ፈቃድ የተሰጠው በጋምቤላ ብሄራዊ ክልል ማጃንግ ዞን፣ ማንግሽ ወረዳ ሲሆን ለፕሮጀክቱ ከ138 ሚሊየን ብር በላይ መመደቡ ተገልጿል፡፡ ይህ ኩባንያ በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ውስጥ 911 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ያመርታል ተብሏል። ሌላኛው ፈቃድ የተሰጠው ተቋም "ኢልኔት ቴክኖሎጂ ግሩፕ" ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ዞን፣ አሶሳ እና ሁዱሉ ወረዳዎች እንደሆነ ተገልጿል። ይህ ኩባንያ ለፕሮጀክቱ ከ148 ሚሊየን ብር በላይ መመደቡ አስታውቋል፡፡ የፈቃዱ የአገልግሎት ዘመን…
Read More