27
Mar
በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ከማዕድን ዘርፍ 252 ነጥብ 15 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል። የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት፤ በ2016 በጀት ዓመት የተለያዩ ዓይነት ማዕድናት ወደ ውጭ ገበያ በመላክ 252 ነጥብ 15 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ባለፉት ስምንት ወራት ከሁለት ሺህ 673 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ፣ 66 ቶን በላይ ታንታለም እና ከ11 ሺህ 176 ቶን በላይ ሉቲየም ኦር ለውጭ ገበያ መቅረባቸውን ዘርዝረዋል። በተጨማሪም ከ99 ሺህ 021 በላይ ቶን የጌጣጌጥ እንዲሁም 29 ሺህ 281 ቶን በላይ የኢንዱስትሪ ማዕድናት ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉን አቶ ሚሊዮን ተናግረዋል። የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት…