tulukapigoldmining

ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ“PW ማይኒንግ” ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ“PW ማይኒንግ” ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

የከፊ ሚኒራልስ ኩባንያ አካል የሆነው ቱሉ ካፒ ጎልድ ማይኒንግ ከእንግሊዙ 'PW ማይኒንግ' ጋር የወርቅ ማዕድን ልማትና በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ የተፈረመው ከትናንት ሚያዚያ 18/2015 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ በሚገኘው፤ “ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023” ዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማትና ባለሃብቶች ፎረም ጎን ለጎን ነው። በፎረሙ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ባለሃብቶች፣ የንግድ ተዋንያን፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ሥራ ፈጣሪዎች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን፤ በመድረኩ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቶች፣ የፓናል ውይይቶች፣ የተመረጡ ኩባንያዎች ጉብኝትና አውደ ርዕይዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨትመንት ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚከናወነው ይህ ፎረም በግብርና፣ ማንፋክቸሪንግ፣ አይ.ሲ.ቲ፣ ማዕድን እና በቱሪዝም ላይ ትኩረቱን አድርጓል። በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨሰትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፣…
Read More