ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 51 ባለሀብቶች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተሰማሩ የውጭ ሀገራት ኢንቨስተሮች በሙስና ምክንያት ከሚሰሩባቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለቀው እየወጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የበጀት ዓመቱን ዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ የምርት ዘርፎች የተሰማሩ የውጭ ሀገራት ኩባንያዎች ከመንግስት ተቋማት መሪዎች እና ባለሙያዎች በሚጠየቁ ክፍያ ምክንያት መማረራቸው ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ የኢንቨስትመንት ኮሚሽኑንን ሪፖርት በገመገመበት ወቅት እንደገለጸው በኦሮሚያ ክልል ዱከም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ ያሉ ኩባንያዎች ቅሬታ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በዚህ ኢንዱስትሪ ፓርክ ባደረጉት ምልከታ ኢንቨስተሮች የሚጠይቋቸውን ከትንሽ እስከ ትልቅ አገልግሎቶች በገንዘብ እየገዙ ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም በፓርኩ ላይ የባለቤትነት ስሜት ባለመኖሩ ፓርኮች ውስጥ እየገቡ ዘረፋ እየተፈጸባቸው መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት በመስክ ምልከታቸው ወቅት መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ በኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ በተሰማሩ ኢንቨስተሮች ላይ በሚፈጸም የስርቆት፣ ሙስና እ ና ቢሮክራሲ ምክንያት የተማረሩ 51 ባለሀብቶች ለቀው መሄዳቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ፓርክ የለቀቁ ባለሀብቶች ከአገር በመውጣት ወደ ኡጋንዳና ሌሎች ጎረቤት አገሮች እና ወደ ሌሎች አገር ውስጥ ወደ ሚገኙ ኢዱስትሪ ፓርኮች መፍለሳቸውን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል ተሬሳ፣ በበኩላቸው በምክር ቤቱ የቀረበው አስተያየት ትክክል አይደለም በሙስና እና በስርቆት ምክንያት ከሀገር የተሰደደ ኢንቨስተር የለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *