Dubaipolice

አረብ ኢምሬት የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለኢትዮጵያ አሳልፋ ሰጠች

አረብ ኢምሬት የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለኢትዮጵያ አሳልፋ ሰጠች

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዱባይ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያውያን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የነበሩ ዳውድ ተፈሪ እና ደስታ ተገኝ የተባሉ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም 105 ዜጎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዱባይ በመውሰድና ከ188 ሚሊየን ብር በላይ ከተጎጂዎች በመሰብሰብ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ የቆዩ በመሆናቸው ከዱባይ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ሥር ውለው ለኢትዮጵያ ተላልፈው እንዲሰጡ ተደርጓል ብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ዱባይ ተቀምጠው ሀገር ውስጥ ባሉ ተባባሪዎቻቸው አማካኝነት ወጣቶችን በመመልመል ወደ ዱባይ በመላክ፣ በተዘጋጀ የማገቻ ቦታ በማቆየት፣ በተለይ በሴቶች ላይ ጥቃት በማድረስና በማሰቃየት ከፍተኛ ወንጀል ሲፈጽሙ የቆዩ መሆናቸው ተረጋግጧል። ፌደራል ፖሊስም ጉዳዩን ሲያጣራ ቆይቶ…
Read More