10
May
ኢትዮጵያ በወንጀል የምትፈልጋቸውን ሰዎች አሜሪካ አሳልፋ እንድትሰጣት ጥያቄ አቅርባለች፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአሜሪካው ኤፍ.ቢ.አይ (FBI) ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አምባሳደሩ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ኮሚሽነሩ በውይያታቸው ወቅት ጠይቀዋል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ በተለይም በአሜሪካን ሀገር እየኖሩ የሀገሪቱን ሰላም እያወኩ ነው በሚል የምትጠረጥራቸውን ሰዎች ተላልፈው እንዲሰጧት ለአምባሳደሩ ጥያቄ እንዳቀረቡም ተገልጿል፡፡ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በአሜሪካን መንግሥት የሚፈለጉ ወንጀለኞችን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አሳልፎ በመስጠት ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ተብሏል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተመሳሳይ ድጋፎችን እንድታደርግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ…