30
Jul
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል እና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር በበርካታ የሀገራችን ወጣቶች ላይ ከባድ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም የቆየውን አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በማላዊ ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል በማድረግ ለኢትዮጵያ ተላልፎ መሰጠቱን አስታውቋል። አድነው ባሻው ውዳሞ በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም ከሀድያ እና ከንባታ ዞኖች በርካታ ወጣቶችን ሕይወት እንደሚያሻሽል በመሐላና በአጉል ተስፋ በማታለል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያዘዋውር መቆየቱን ፖሊስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል። ተጠርጣሪው ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ…