Migration

በአማራ ክልል ያለው ስደት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

በአማራ ክልል ያለው ስደት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

የአማራ ክልልን ለቆ ወደ ስደት እና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚፈልሰው የክልል ተወላጅ መጠን "አጅግ አስደንጋጭ " መሆኑን የክልሉ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ። በአማራ ክልል ባለፉት 5 ወራት ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች 36 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል። ይህ የተነገረው የትምህርት ቢሮው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ላይ የ5 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት እንደሆነ ሸገር ኤፍኤም ዘግቧል። የምክር ቤቱ አባላት ለተማሪዎች በትምህርት ገበታ አለመገኘት ጦርነቱን፣ ስደት፣ የቀን ስራ፣ በትምህርት ተስፋ መቁረጥን ጨምሮ የተለያዩ ምክንያቶችን ዘርዝረዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ ትምህርት ያልተመለሱ ተማሪዎች አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን መረጃ ማግኘት እንዳልተቻለ አስረድተዋል። አንድ የምክር…
Read More
ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በ38 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በ38 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

​የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የጥቅምት 2025 ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ስድስት የድንበር ፍሰት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ የታየው የሰዎች እንቅስቃሴ ካለፈው መስከረም ወር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። በወሩ ውስጥ በአጠቃላይ 45,150 የሰዎች ዝውውር የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በቀን በአማካይ 1,456 ሰዎች ድንበር እንደሚያቋርጡ ያሳያል ነው የተባለው። ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አብዛኛው ማለትም 78.3 በመቶው (35,341 ሰዎች) ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚወጡ ሲሆን፣ ቀሪው 21.7 በመቶው (9,809 ሰዎች) ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ናቸው። በጥቅምት ወር ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ካለፈው የመስከረም ጋር ሲነጻጸር የ38 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሪፖርቱ አመላክቷል። ይህ የፍልሰት መጨመር በተለይ በሱዳን ድንበር በሚገኘው በመተማ በኩል በከፍተኛ ሁኔታ የታየ…
Read More
ኢትዮጵያ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎቿን ከውጭ ሀገራት መመለሷን ገለጸች

ኢትዮጵያ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎቿን ከውጭ ሀገራት መመለሷን ገለጸች

ከመስከረም ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ ሀገር መመለሳቸው ተገልጿል። በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ዜጎችን ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎችን ከመስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተሰራ ሥራ መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ "ከውጭ ግንኙነት ቁልፍ ሥራዎች አንዱ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ነው" ያለው ሚኒስቴሩ ፖሊሲውን በአግባቡ ለመተግበር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎችን መብት ማስከበር፣ ለዜጎች ተገቢ የቆንስላ አገልግሎት መስጠት፣ በሄዱበት ሀገር ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውና የሀገሩ መንግሥት ዜጎቻችን ሀገራቸውን እንዲለቁ ሲወስን መብታቸው፣ ክብራቸውና…
Read More
ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ለማያውቁት ሀገር ለውትድርና እየተመለመሉ ነው ተባለ

ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ለማያውቁት ሀገር ለውትድርና እየተመለመሉ ነው ተባለ

‎መደበኛ ባልሆነ እና በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የሚፈልሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማያውቁት ሀገር ለውትድርና እየተመለመሉ ነው ሲሉ በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ ተናግረዋል። በተጨማሪም ሕገ-ወጥ ፍልሰተኞቹ ከሚያጋጥሟቸው የከፉ ችግሮች መካከል፤ እሥር፣ የወሲብ ባርነት፣ መደፈር፣ ከባድ አካላዊ ቅጣት፣ አካል ጉዳተኝነት፣ እንደ ኩላሊት ያሉ የውስጥ አካልን በግዳጅ መዘረፍ እንደሚገኙበት ገልጸዋል። ይሁንና ሚንስትሯ ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ለየትኛው ሀገር በውትድርና እንደተመለመሉ አልጠቀሱም። ኢ-መደበኛ በሆነ መንገድ ከሀገር የሚወጡት ዜጎች ከአካል ጉዳት እና የግዳጅ ውትድርና በተጨማሪ፤ ለአዕምሮ ጤና እክል እና ለሥነ-ልቦና ቀውስ ተጋላጭ እንደሚሆኑም ተነስቷል። ሚኒስትር ደኤታዋ አያይዘውም፤ የሰው ልጅ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ፍላጎቶችን ለማጣጣም ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሱ ግድ ቢሆንም፤ እንቅስቃሴው ሕጋዊ መስመርን…
Read More
ከ800 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት መሰደዳቸው ተገለጸ

ከ800 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት መሰደዳቸው ተገለጸ

ባለፉት አምስት ዓመታት ከ800 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት ፈልሰዋል የተባለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 78 በመቶ የሚሆኑት ወጣት ከመሆናቸውም በላይ አብዛኞቹ ሴቶች መሆናቸው ተነግሯል ። የኢትዮጵያ ዜጎች በስራ ዕድል እጦት የተነሣ በተለያዩ መተላለፊያዎች ድንበር አቋርጠው እንደሚፈልሱ የተገለፀ ሲሆን ድህነት ፣ የሰላም እጦት፣ የመነሻ ሐብት ምንጭ እጥረት ፣ የአየር ንብረት መለዋወጥና የተፈጥሮ ውድመት ዋና ዋና ገፊ ምክንያቶች እንደሆኑ ተገልጿል ። በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊያን ድንበር አቋርጠው እንዲፈልሱ ሳቢ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል ለራሳቸውና ቤተሰባቸው ገቢ የማመንጨት  ፍላጎት መኖር እና  የተሻለ ህይወት ፍለጋ እንደሆነ ይጠቀሳሉ ተብሏል ። የኢትዮጵያ ፍልሰተኛ ሰራተኞች ለኢትዮጵያ መልካም ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሲሆን ሀገሪቱ ውጭ ከሚኖሩና ከሚሰሩ ዜጎቿ ዳጎስ…
Read More