12
Dec
በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች በመንግሥት እየተዋከቡ ነው መባሉን የስደተኞችና ተመላሾች አግልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል፡፡አገልግሎቱ በመግለጫው በኢትዮጵያ የተጠለሉ ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም ብሏል፡፡ ከሰሞኑ እንደ በርካታ አለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጨምሮ በስፋት የተዘገበው የኤርትራዊያን በአዲስ አበባ መዋከብ ከእውነታው የራቀ ነው በማት አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ በሚገኙ በኤርትራውያን ላይ የጅምላ እስራት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ከሰሞኑ ሲዘገብ ነበር፡፡ ምንም እንኳን መሰል ክስተቶች አዲስ ባይሆኑም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የጅምላ እስራት ግን ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ኤርትራውያን ከሰሞኑ ለቪኦኤ መናገራቸው ይታወሳል።ይሁን እንጂ የስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው አገልግቱ በሰጠው ምላሽ በኢትዮጵያ የሚገኙ…