22
Mar
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮያውያንን ወደ ሀገራቸው እመልሳለሁ ብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ “በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 70 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው የመመለስ ሦስተኛ ምዕራፍ በሁለት ሳምንት ውስጥ ይጀምራል” ብለዋል። በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኘው ኢትዮያውያንን ለመመለስ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ መክሯል። የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፤ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሥራ በብሔራዊ ኮሚቴው ውስጥ የታቀፉት የፌዴራል ተቋማት እና የክልሎችን የጋራ ቅንጅት ይጠይቃል ብለዋል። ከወዲሁ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በተሟላ ሁኔታ በፍጥነት መጠናቀቅ እንደሚገባቸውም አምባሳደር ብርቱካን ተናግረዋል። አምባሳደር…