12
Jun
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት የዓለም ሥራ ድርጅት አስተዳድር አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በጀኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው የዓለም ሥራ ድርጅት (ILO) 112ኛ ጉባኤ ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው ስብሰባ ለቀጣይ 3 ዓመታት በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚያስተዳድሩ አካላትን ከሠራተኞች ፣ከመንግሥታትና ከአሠሪዎች መካከል ለመምረጥ ባደረገው እንቅስቃሴ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ባገኙት ከፍተኛ ድምፅ የዓለም ሥራ ድርጅት የሚያስተዳድረው አካል አባል በመሆን መመረጣቸው ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ 112ኛ ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 30 ቀን 2016 ባካሄደው ስብሰባው የዓለም ሥራ ድርጅትን በበላይነት የሚያስተዳድር (Governing Body) ምክትል አባል ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን አንዷ አድርጎ መርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከተወዳደሩት ሰባት ሀገራት…