16
Sep
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን እንዲወስን በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቦ ነበር የገንዘብ ሚኒስቴር ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ 91.4 ቢሊየን ብር በጀት ይፋ ተደርጓል፡፡ መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ከአንድ ወር በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ የደመወዝ ጭማሪ 2.3 ሚሊየን የፌደራልና የክልል መንግስታት የመንግስት ሰራተኞች፣ 56 ሺህ ተሿሚዎች፣ ለሀገር ደህንነት ሲባል ቁጥራቸው የማይቀመጠው የክልል ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የደሞዝ ማሻሻያው ተጠቃሚ ናቸው ተብሏል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ለዝርዝር የደሞዝ መግለጫው በፃፉት መግቢያ "በተለይም ዝቅተኛ የደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ እና ሊደርስ የሚችለውን የኑሮ ጫና በመጠኑም ቢሆን ለመቋቋም እንዲችሉ" የሚል አገላለፅ ተጠቅመዋል፡፡ በጭማሪው…