salaryinethiopia

የመንግስት ተቋማት ስራ ለለቀቁና ለሞቱ ሰራተኞች ከ400 ሺህ በላይ ብር ደመወዝ ከፍለዋል ተባለ

የመንግስት ተቋማት ስራ ለለቀቁና ለሞቱ ሰራተኞች ከ400 ሺህ በላይ ብር ደመወዝ ከፍለዋል ተባለ

የፌደራል ዋና ኦዲተር የመንግስት ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የበጀት ኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ዋና ኦዲተር በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው 17 የመንግስት ተቋማት በጡረታ፣ በሞትና በሌሎች ምክንያት ከሥራ ለለቀቁ ሰራተኞች 408,462 ብር ያላግባብ ደመወዝ ከፍለው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ  በስተቀር የሰራተኞች ቅጥር፣ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር እንዳይፈጸም ቢከለክልም በስምንት መስሪያ ቤቶችና በአንድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በጠቅላላው 24,073,003 ብር የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ሳያስፈቅዱ በቋሚ የሥራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን በኮንትራት በመቅጠር ክፍያ ፈጽመዋልም ተብሏል፡፡ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን ሳያስፈቅዱ የኮንትራት ቅጥር ከፈጸሙት ተቋማት መካከል የቅደስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ፣ ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ፣…
Read More
ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰኛ ጊዜን አራዘመች

ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰኛ ጊዜን አራዘመች

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን እንዲወስን በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቦ ነበር የገንዘብ ሚኒስቴር ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ 91.4 ቢሊየን ብር በጀት ይፋ ተደርጓል፡፡ መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ከአንድ ወር በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ የደመወዝ ጭማሪ 2.3 ሚሊየን የፌደራልና የክልል መንግስታት የመንግስት ሰራተኞች፣ 56 ሺህ ተሿሚዎች፣ ለሀገር ደህንነት ሲባል ቁጥራቸው የማይቀመጠው የክልል ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የደሞዝ ማሻሻያው ተጠቃሚ ናቸው ተብሏል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ለዝርዝር የደሞዝ መግለጫው በፃፉት መግቢያ "በተለይም ዝቅተኛ የደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ እና ሊደርስ የሚችለውን የኑሮ ጫና በመጠኑም ቢሆን ለመቋቋም እንዲችሉ" የሚል አገላለፅ ተጠቅመዋል፡፡ በጭማሪው…
Read More