Employment

በኢትዮጵያ የስራ ማቆም አድማ ሊደረግ እንደሚችል ተገለጸ

በኢትዮጵያ የስራ ማቆም አድማ ሊደረግ እንደሚችል ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አባል ማህበራት የሰራተኞች ጥያቄ ካልተመለሱ  ስራ የማቆም አድማና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በመንግስት እንዲወሰንና ከደመወዝ ላይ የሚቆረጠው ከፍተኛ_ግብር እንዲቀንስ መንግስት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ምላሽ አልሰጠም ተብሏል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሰራተኞች ወደ ስራ ማቆም አድማና ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያመሩ እንደሚችሉ ማህበራቱ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የኢትዮጵያን ሰራተኞች ይወክላሉ ከሚባሉት አባላቱ ጋር ባሳለፍነው ሳምንት አድርጎት በነበረው ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ አባላቱ በሰራተኞች ጥቅም ዙሪያ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ማህበራቱ በመግለጫቸው እስካሁን ስናነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎቻችን በመንግስት ባለመመለሳቸው ከዚህ በኋላ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንዲሁም በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንገደዳለን ማለታቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የውጭና ህዝብ…
Read More
በውጭ ሀገራት የተቀጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ደህንነት ለማስከበር ያለመ ስምምነት ተፈረመ

በውጭ ሀገራት የተቀጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ደህንነት ለማስከበር ያለመ ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሠሪ ፌዴሬሽን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመዋል፡፡ ስምምነቱ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሠሪ ፌዴሬሽን በውጭ ሀገር በሥራ የሚሰማሩ ዜጎችን መብት እና ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ ነው፡፡ በስምምነቱ ወቅት የፌዴሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ፣የዓለም ሥራ ድርጅት ተወካይ እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ በፊርማው ሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ኮንፌዴሬሽኑ በሀገር ውስጥ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች መብቶች እንዲከበሩ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ከሀገር ውስጥ በተጨማሪም በውጭ ሀገራት ተቀጥረው የሚሠሩ ኢትዮጵያዊን መብታቸው ተጠብቆ እዲሠሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ…
Read More
ኩዌት ኢትዮጵያዊን ሰራተኞችን ለመቅጠር ተስማማች

ኩዌት ኢትዮጵያዊን ሰራተኞችን ለመቅጠር ተስማማች

ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢ ፈርመውታል። በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሠለሞን ሶካ እና ዳንኤል ተሬሳ፣ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሁመድ፣ በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢን ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ስምምነቱ ወደ ኩዌት የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅማቸው ተጠብቆ ህጋዊ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን የትብብር ሁኔታ እንደሚፈጥር ተገልጿል። በነዳጅ የበለጸገችው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር ኩዌት የሦስት ወራት አስገዳጅ ስልጠና የወስዱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን…
Read More