26
Mar
የመንግስት እና የግል ተቋማት ከሚሰጧቸው የተለያዩ አገልግሎቶች “ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” የሚሆን ገቢ እንዲሰበስቡ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ባሳለፍነው ሳምንት ለፓርላማ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ሳይወስን ገንዘብ ለመሰብሰብ አዲስ ረቂቅ ማስተዋወቁ ማንም አይጠይቀኝም ከሚል የመነጨ ነው ብሏል፡፡ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስን በፓርላማ የፀደቀውን አዋጅ ሳያስተገብር ከሰራተኛው ላይ ገንዘብ ለመሰብሰብ አዲስ ረቂቅ ማስተዋወቁ ማንም አይጠይቀኝም ከሚል የመነጨ ነውም ብሏል። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን እንደ አዲስ እንዲቋቋም የታሰበው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ለተቀጣሪ ሰራተኞች ራሱን የቻለ አደጋ ነው ብሎታል። ከሳምንት በፊት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጁ የቀረበው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋትና ስራ…