wages

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች በወሲብ ንግድ መሰማራታቸው ተገለጸ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች በወሲብ ንግድ መሰማራታቸው ተገለጸ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ኑሮን ለማሸነፍ ስላላስቻላቸው ማታ ማታ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ መኖራቸውን በጥናት መለየቱን የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ትርፍራፊ ምግቦችን ይዘው ወደ ቤታቸው የሚገቡ እንዳሉም ፌደሬሽኑ ጠቁሟል፡፡ አምራች ስራተኛ፣ ምቹ ስራ ለወጣቶች እና ሴቶች በጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ መፍጠር በሚል ርዕስ የፖሊሲ አቅጣጫ ጠቋሚ ጥናት ለማድረግ የማህበራት ጥናት መድረክ (Forum For Social Studies) በጠራው የሁለተኛ ዙር የባለድርሻ አካላት ወይይት ላይ የተገኙት የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ ተስፋዬ አብዲሳ ‘’የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ተመላሽ ምግቦችን ይዘው የሚገቡ እንዳሉም በጥናት…
Read More
ኢሰማኮ ለሰራተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ ጠየቀ

ኢሰማኮ ለሰራተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ እንዳሉት በቋሚ ደመወዝ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ሌሎች የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን በደብዳቤ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ እንደገለጹት ከብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተያይዞ ቋሚ ደመወዝ የሚያገኙ ሰራተኞች ለከፍተኛ የኑሮ ውድነት መዳረጋቸውን ገልጸዋል። "በተለይም ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኘው ሰራተኛ ቀን ቀን እየሠራ ማታ ማታ ሆቴሎች ላይ ፍርፋሪ እየለመነ እያደረ ነው።" ያሉት ፕሬዝዳንቱ የኑሮ ጫናው በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረው በሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። አክለውም ከዚህ በፊት በሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ ዙርያ ከጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ጋር ተደጋጋሚ  ውይይቶች መደረጋቸውን አስታውሰው ነገር ግን እነዚህ ውይይቶች ውጤት…
Read More