30
May
የዳሽን ባንክ ሐዋሳ ቅርንጫፍ ባለሙያ የሆነችው ፀጋ በላቸው በሐዋሳ ከንቲባ ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደማርያም መጠለፏ ተገልጿል። የሲዳማ እና ደቡብ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ሀዋሳ ከተማ ይህ መፈጸሙ ብዙዎችን ያስደነገጠ ድርጊት ሆኗል። ባለሙያዋ በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ተጠልፋ ከተወሰደች ከሳምንት በላይ ሆኗታል። የተጎጂዋ ቤተሰቦች እንዳሉት የግል ተበዳይ በቤተ ክርስቲያን ደንብ መሰረት የጋብቻ ትምህርት ከወደፊት የትዳር አጋሯ ጋር ተምረው በማጠናቀቅ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ለመጋባት ቀን ቆርጠው የቤት ዕቃዎችን በማሟላት ላይ ነበሩ። ይሁን እንጂ ጥቃት አድርሷል በሚል በፖሊስ የሚፈለገው ተጠርጣሪ የግል ተበዳይን በተደጋጋሚ ይዝትባት እና ያስፈራራት እንደነበር ቤተሰቦቿ ተናግረዋል። የግል ተበዳይ ቤተሰቦች ፀጋ ያለችበትን ባለማወቃቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ…