13
Jan
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲ አበባ የታጠቁ ድሮኖችን ለጸጥታ ስራ እንደሚጠቀም አስታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ አስተዳደር የከተማዋን ፀጥታ ሁኔታና ትራፊክ ፍሰት ለመቆጣጠር ይሰማራሉ የተባሉ ድሮኖች ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን እርምጃም እንደሚወስዱ አስታውቋል። የትራፊክ ፍሰት እና በበዓላት ወቅት የከተማዋን ጸጥታ ለመቆጣጠር በርካታ ድሮኖች መግባታቸው እና የሚቆጣጠሯቸው ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ስልጠና አጠናቅቀው በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡ ድሮኖቹ የከተማዋን ፀጥታ ሁኔታና የትራፊክ ፍሰት ከመቆጣጠር ባሻገር እርምጃም እንደሚወስዱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል፡፡ በቅርብ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ፍሰትና አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ታላላቅ ፕሮግራሞችን ቁጥጥር ማድረግ የሚችሉ የድሮኖች ስምሪት እንደሚደረግ፣ የፀጥታ ጥምር ግብረ ኃይል ከቀናት በፊት መግለጹ ይታወቃል፡፡ አሁን ላይ በርካታ ድሮኖች…