15
Mar
ኢትዮጵያ ከ128 ዓመት በፊት ለተካሄደው የጸረ ቅኝ ግዛት ትግል ድል ያደረገችበት የአድዋ ድል ሙዚያምን ከሶስት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ በይፋ ማስመረቋ ይታወሳል፡፡ ከ4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ይህ ሙዚየም ከነገ መጋቢት ስድስት ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ በዚህም መሰረት ይህንን ሙዚየም ለመጎብኘት በግለሰብ ደረጃ 150 ብር መክፈል ግዴታ ሲሆን ለተማሪዎች 75 ብር እንዲሁም ለልዩ ልዩ ጎብኚዎች ደግሞ 500 ብር ዋጋ ተተምኖለታል፡፡ ጎብኚዎች ሙዚየሙን መጎብኘት የሚችሉት ከጠዋት 2:30 እስከ አመሻሽ 11:30 ሰዓት ድረስ እንደሆነም ከመታሰቢያ ሙዚየሙ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ ለሙዚየሙ ከተቀመጡ ማስታወሻዎች መካከል ለድሉ አስተዋጽኦ ያደረጉ የጦር መሪዎች መታሰቢያ ሀውልት እና ተቋማት ስያሜ ባለፈ የራሱ ሙዚየም…