Eotc

ቤተ ክርስቲያኗ በትግራይ ክልል ያሉ የአራት ሊቀ ጳጳስን ክህነት አነሳች

ቤተ ክርስቲያኗ በትግራይ ክልል ያሉ የአራት ሊቀ ጳጳስን ክህነት አነሳች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ክልል የተሰጠው ኤጲስ ቆጵሳት ሹመት ህገወጥ መሆኑን አስታውቃለች። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፌያለሁ ብሏል። ቤተ ክርስቲያኗ አክላም ከፍተኛውን ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲወጡ አደራ በተሰጣቸው ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበረሰብ ዕድገትና አስተዳደር ውስጥ ከሕዝብ ጋር በቆመች፣ ከፖለቲካ በጸዳች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ መንፈሳዊና ሕዝባዊት ተቋምነቷን በመካድ ከፍተኛ የሆነ ሕገ ወጥ ድርጊትና ተቋምን የመናድ እንደሁም መዋቅሯን የማፍረስ ተግባር ተከናውኖብኛል ብላለች። ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ/ም በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም ውስጥ የተፈጸመውን ሕገወጥ የሆነ አስነዋሪ፤ የቀኖና ቤተ…
Read More
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትግራይ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትግራይ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀች

ቤተ ክርስቲያኗ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳትን እንደምትሾም አስታውቃለች ቤተክርስቲያኗ ባወጣችው መግለጫ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ በተፈጸመው ሲመት በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ የደረሰውን መከራና ፈተና ለማሳለፍ ሲባል ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን እና ትውፊቷን ባስጠበቀ ሁኔታ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ትረት ስታደርግ መቆየቷን ገልጻለች። በዚህ መሰረትም የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ቀኖናዋን ከስምምነቱ ፤ ስምምነቱን ከቀኖናዋ ጋር በማዛመድ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል ባሉ ክፍት አህጉረ ስብከት ተመድበው የሚያገለግሉ 9 ኤጲስ ቆጶሳት በቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲሾሙ…
Read More
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳት እንዲሾሙ ወሰነች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳት እንዲሾሙ ወሰነች

ላለፉት አምስት ቀናት በደዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቋል። በጉባኤው የማጠቃለያ ፕሮግራም ችግር ባለባቸው እና አስፈላጊ በሆኑባቸው አህጉረ ስብከት 9 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ  ውሳኔ አሳልፏል። የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። አቡነ ጴጥሮስ አክለውም "የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሰላም እና ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል፣ ዛሬ የመጨረሻው አጀንዳ ላይ ብዙ ውይይት ተካሂዷል፣ በመጨረሻ ሁሉም አባቶች ተወያይተው ቤተክርስቲያንን የሚጠቅመው ምንድነው ? የሚለው ላይ በመምከር ውሳኔ ተላልፏል" ብለዋል። "የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲካሄድ ተወስኗል። የመጀመሪያው ችግር ያለባቸው ሀገረ ስብከት የሚል ሲሆን ይህንን የሚያስፈጽምም 7 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል…
Read More
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የ23 የቀድሞ አባቶችን ውግዘት አነሳች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የ23 የቀድሞ አባቶችን ውግዘት አነሳች

ቤተ-ክርስቲያኒቱ ከህግ ውጭ ሲመተ ጵጵስና የሰጡና የተቀበሉ 26 የቀድሞ አባቶችን ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ማውገዟ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ጳጳሳትንና የ20 መነኮሳትን ውግዘት አንስቷል። ውግዘቱ የተነሳው ከዛሬ መጋቢት 21፤ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ ምልዓተ ጉባኤው አሳውቋል። ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው "ሦስቱም የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ላይ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተነስቷል" ብሏል፡፡ በቀድሞ የሊቀ ጳጳስነት ማዕረጋቸው እንዲጠሩና ተመድበው ይሰሩበት በነበረው የስራ ኃላፊነታቸው እንዲቀጥሉም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ የየካቲት ስምንቱን ባለ10 ነጥብ ስምምነት እንቀበላለን ብለው ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ ያስገቡ 20 የቀድሞ አባቶች ውግዘትም…
Read More
የትግራይ አህጉረ ስብከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትን እንዲያከብር ቋሚ ሲኖዶስ ጠየቀ

የትግራይ አህጉረ ስብከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትን እንዲያከብር ቋሚ ሲኖዶስ ጠየቀ

የትግራይ አህጉረ ስብከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትን እንዲያከብር ቋሚ ሲኖዶስ ጠየቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ከሰሞኑ በትግራይ አህጉረ ስብከት በተሰጠ መግለጫ ዙሪያ ምላሽ ሰጥታለች። ቤተ ክርስቲያኗ በመግለጫዋ እንዳለችው በጦርነቱ ምክንያት በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ መዋቅርና በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት መካከል አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ግንኙነት ተቋርጦ መቆየቱን ገልጻለች። ይህንንም ተከትሎ በጦርነቱ ምክንያት ሁሉም የባንክ ተቋማት ሥራቸውን በማቆማቸው በየጊዜው እንደሌሎች አህጉረ ስብከት ለትግራይ አህጉረ ስብከት ይላክ የነበረው በጀት መላክ አልተቻለም ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ እርምጃ ምንድን ነው? ቤተክርስቲያኗ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር በቀኖናው መሰረት መፈታቱን ገለጸችምንም እንኳን በባንክ መዘጋት ለአገልጋይ ሠራተኞች በጀት መላክ ባይቻልም የደመወዝ መክፈያ የባንክ…
Read More
በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙ ጳጳሳት አህጉረ ስብከቶችን መልቀቃቸው ተገለጸ

በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙ ጳጳሳት አህጉረ ስብከቶችን መልቀቃቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አገረ ስብከት በሦስት አባቶች ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ በሆነ መልኩ ለ25 አባቶች ሕገ ወጥ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት መሰጠቱ አይዘነጋም፡፡ ይህን ተከትሎም ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 18 ቀን 2015 በጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባዔ፣ እነዚህን አካላት ከቤተክርስቲያን ሕብረት ለይቶ ማውገዙ፣ እንዲሁም በየትኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ እንዳይገኙ የእግድ ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡ ችግሩ በእርቅ ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኩል በተደረገው ስምምነት መሰረት፣ በሹመቱ የተካተቱ አካላት ወደ ቀድሞ ሥማቸው እንዲመለሱ ስምምነት ከተደረገ በኋላም፤ ጉዳዩ በስምምነቱ መሰረት አለመፈጸሙን ቤተክርሰውቲያኗ በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡ ሕገ ወጥ የተባሉት ተሹዋሚዎች ከስምምነቱና ከሲኖዶስ ውሳኔ አፈንግጠው፣ ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች በተለይም በወለጋ…
Read More
በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ህግ በጣሱ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ህግ በጣሱ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ህግ በጣሱ የፖሊስ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ። በዘንድሮው የአድዋ በኣል በአዲስ አበባ ምኒልክ አደባባይ የጸጥታ ሀይሎች በዜጎች ላይ ያልተገባ ድርጊት መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና ሌሎችም ተቋማት መናገራቸው ይታቀሳል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዪ ዙሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በዕለቱ የህግ ጥሰት በፈጸሙ የፖሊስ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። ኮሚሽኑ አክሎም በዓሉ በተከበረበት እለት የከተማዋን ሰላም አውከዋል በሚል 878 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውያለሁ ብሏል። በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም 557ቱ ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን…
Read More