Ruleoflaw

በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ህግ በጣሱ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ህግ በጣሱ ፖሊሶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ህግ በጣሱ የፖሊስ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ። በዘንድሮው የአድዋ በኣል በአዲስ አበባ ምኒልክ አደባባይ የጸጥታ ሀይሎች በዜጎች ላይ ያልተገባ ድርጊት መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና ሌሎችም ተቋማት መናገራቸው ይታቀሳል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዪ ዙሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በዕለቱ የህግ ጥሰት በፈጸሙ የፖሊስ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል። ኮሚሽኑ አክሎም በዓሉ በተከበረበት እለት የከተማዋን ሰላም አውከዋል በሚል 878 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውያለሁ ብሏል። በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም 557ቱ ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን…
Read More