kirkossubcity

በአዲስ አበባ አንድ የወረዳ አመራር በፖሊስ ተገደሉ

በአዲስ አበባ አንድ የወረዳ አመራር በፖሊስ ተገደሉ

በአዲስ አበባ አንድ የወረዳ አመራር በፖሊስ ተገደሉ በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አለባቸው አሞኜ በቢሯቸው ውስጥ በአዲስ አበባ ፖሊስ አባል ተገደሉ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል ነው፡፡ የፖሊስ አባሉ የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለከተውን ማመልከቻ ለመከታተል ወደ ወረዳው መጽህፈት ቤት መሄዱን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ የወረዳው ስራ አስፈጻሚም ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ በሚል ምክንያት ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ መግደሉን…
Read More
በአዲስ አበባ የአንድ ወረዳ ስራ አስፈጻሚ ተገደሉ

በአዲስ አበባ የአንድ ወረዳ ስራ አስፈጻሚ ተገደሉ

በአዲስ አበባ የአንድ ወረዳ ስራ አስፈጻሚ ተገደሉ በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አለባቸው አሞኜ በቢሮአቸው ውስጥ ተገደሉ። የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ባሰራጨው መረጃ ፤ " አቶ አለባቸው አሞኜ ቢሯቸው ውስጥ ቁጭ ብለው የህዝብ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከአንድ ተገልጋይ በሽጉጥ ተገድለዋል። ክፍለ ከተማው ስለ ግድያው ተጨማሪ መረጃ ባያደርግም ግድያውን ፈጽማል የተባለለው ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል። ክፍለከተማው ባወጣው መግለጫ " አቶ አለባቸው በስራ ቁርጠኝነት የሚታወቁ ናቸው" "በበርካታ መንግስታዊና ህዝባዊ ተግባራት አርዓያነት ያለው ስራ የሰሩና ያስተባበሩ አመራራችን ነበሩ " ሲል ገልጿል። አመራሩ በደረሰባቸው ጥቃት ወደ ህክምና ቦታ ቢወሰዱም ህይወታቸውን ማትረፍ እንዳልተቻለ ተገልጿል።
Read More