21
Oct
የታክሲ ኮንትራት በመጥራት ሹፌሮችን በመግደል ተሽከርካሪ ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላለፈባቸው በተለያዩ ጊዜያት አሽከርካሪዎችን ራቅ ወዳለ ስፍራ እየወሰዱ በመግደል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል። በአዲስ አበባ ገላን ክፍለ ከተማ፣ በሳሪስ እንዲሁም በቢሾፍቱ መኖሪያቸውን ያደረጉት ቴዎድሮስ ብርሃኔ እና እዩኤል ቴዎድሮስ እንዲሁም በሌላ በኩል ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ የተባሉት ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ በመመላለስ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር የሸገር ከተማ አስተዳደር ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ዓቃቢ ህግ አቶ ሚዴቅሳ አጋሩ ተናግረዋል። አራት ግለሰቦች ከግል ተበዳዮች በኮንትራት በመውሰድ ከዋናው መንገድ ውጪ በማስውጣት የአሽከርካሪዎቹን ህይወት በማጣፋት ተሽከርካሪዎቹን ይዞ በመሰወር ለተለያዩ ጋራዦች እና ግለሰቦች በመሸጥ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር ተገልጿል። ቴዎድሮስ እና…