Ethiopianinsaudiarabia

ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ዜጎቿ ደህንነት እንዲጠበቅ መጠየቋ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ዜጎቿ ደህንነት እንዲጠበቅ መጠየቋ ተገለጸ

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ መጠየቃቸው ተገልጿል። ሚንስትሩ ጌዲዮን ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፣ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። ጌዲዮን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች ሕጋዊ የሥራ እድሎችን እንዲያመቻችም መጠየቃቸውን ሚንስቴሩ ጠቅሷል። ሚንስትር ዋሊድ፣ ሕጋዊ የሠራተኞች ፍልሠት ኢትዮጵያዊያን ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ቅጥር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል። የሳዑዲ ዓረቢያ ፍርድ ቤት ከአደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ የሞት ቅጣት የጣለባቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በውይይቱ ወቅት ይነሳ አይነሳ መረጃው አላመለከትም። በየ ዓመቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ…
Read More
ሁለት ኢትዮጵያዊያን በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሁለት ኢትዮጵያዊያን በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሳዑዲ አረቢያ ሁለት ኢትዮጵያውያን አንድ ህንዳዊ በመግደል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል። የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት በቅርቡ በጂዳ ከተማ 'አንድ ህንዳዊ ዜጋ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለዋል' ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ የጂዳ ግዛት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፤ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ደንቦች በመጣስ በሕገ-ወጥ መንገድ በሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል። በከተማዋ አቅራቢያ በሚገኝ ተራራማ አካባቢ ሕገ-ወጥ ዕፅ በመገበያያት ላይ በነበሩ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ጠብና አለመግባባት ሳቢያ ህንዳዊው ግለሰብ በጥይት መመታቱን ገልፍ ኒውስ ዘግቧል፡፡ በዚህም በግጭቱ ወቅት ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ ኢትዮጵያዊ በህንዳዊው ተጎጂ ላይ ተኩስ ከፍቶ ጉዳት እንዳደረሰበት የገለጸው ፖሊስ፤ በጥይት የተመታው ግለሰብ ወዲያውኑ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ቢወሰድም፣…
Read More