24
Jul
የአፍሪካ የሰዎችና ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተላለፉ ፍርዶችና የሞት ቅጣቶች እንደገና እንዲታዩ "ሁሉንም መንገዶች" እንዲጠቀምና የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን ኢትዮጵያዊያን ደኅንነት ለማስከበር አስፈላጊ "የዲፕሎማቲክ" እና "የቆንስላ" ርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቋል። ተቋሙ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ላይ የተጣለው የሞት ቅጣት በእጅጉ እንዳሳሰበው አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያዊያኑ "የሕግ ውክልና" እና የፍርድ ቤት "የትርጉም አገልግሎት" እንዲያገኙና ከቤተሰባቸው ጋር እንዲገናኙ ጥረት እንዲያደርግ፤ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሠተኞችን መብት "በሁለትዮሽ ግንኙነቶች" እና በጠንካራ "የቆንስላ ድጋፎች" እንዲያስከብርም ኮሚሽኑ ጠይቋል። ሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ በስፋት ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በያዝነው ዓመት ብቻ ቢያንስ 12 ኢትዮጵያዊያን የሞት ፍርድ ተፈጽሞባቸዋል። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ድርጅት…