05
Jul
ፖሊስ በአዲስ አበባ ወላጅ አባቱን በቤንዚን አቃጥሎ የገደለን ተጠጣሪ መያዙን ገልጿል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ቤተሰቦቼ ለእኔ ምንም ቦታ የላቸውም በሚል ምክንያት ወላጅ አባቱንና ታላቅ ወንድሙን ቤንዚል በመርጨት በቁም ያቃጠላቸው ተከሳሽ በቁጥጥር ማዋሉን ገልጿል። ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ክብረ ደመና ሙሉ ወንጌል አካባቢ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ነው ተብሏል። ተከሳሹ ከዚህ ቀደም በሌላ ወንጀል ተከሶ ታስሮ የነበረና በፍርድ ቤት ዋስትና የተለቀቀ እንደነበር የገለጸው ፖሊስ ከእናቴ በስተቀር ለእኔ የሚያስብልኝ የለም በሚል ምክንያት ወንጀሉን ለመፈጸም እንደተነሳሳም ተገልጿል። ከሳምንት በፊትም በአንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር ቤንዚል በመግዛት አባቱና ታላቅ…