Dejencity

የደጀን ከተማ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው ተገደሉ

የደጀን ከተማ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው ተገደሉ

በአማራ ክልል፤ የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው “በግለሰብ በተፈጸመባቸው ጥቃት” ህይወታቸው አለፈ። በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በተከፈተባቸው ተኩስ ሲገደሉ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ለወረዳዋ ፖሊስ አዛዦች ህልፈት ምክንያት የሆነውን ተኩስ ከፍቷል የተባለ ተጠርጣሪን ለመያዝ ፍለጋ እየተከናወነ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ጥቃት የተፈጸመባቸው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 26፤ 2015 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ እንደሆነ የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ጋሻዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የፖሊስ አዛዦቹ ላይ ተኩስ የተከፈተባቸው፤ በዛሬው ዕለት በተለያዩ አካባቢዎች…
Read More