18
Dec
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “የክሪፕቶ አሴትን” እና የዲጂታል ገንዘብን በኢትዮጵያ መጠቀም የሚያስችል መመሪያ በቀጣይ ሊያወጣ እንደሚችል ገልጿል፡፡ የተቋሙ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እንደገለጹት ብሔራዊ ባንክ የክሪፕቶ ከረንሲ መመሪያውን የሚያወጣው በማዕከላዊ ባንኪንግ፣ በገንዘብ ፖሊሲ እና በገንዘብ አስተዳደር ያሉ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን እያየ መሆኑን ተናግረዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ16 ዓመት በፊት የወጣውን እና በስራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅን አጽድቋል፡፡ በምክር ቤቱ ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት አቶ ማሞ አዲሱ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ድንጋጌዎች መካከል ክሪፕቶ ከረንሲ እና የዲጂታል ገንዘብን መጠቀም የተመለከቱት ይገኙበታል፡፡ የጸደቀው አዋጅ “አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ብሔራዊ ባንክ ካልፈቀደ በስተቀር፤ ክሪፕቶ ከረንሲ ወይም ሌላ ማንኛውንም ዲጂታል…