01
Nov
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ለጎረቤት አገራት ከሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ከ31 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱን አስታወቀ። ተቋሙ ለጅቡቲ ከሸጠው ከ169 ሺሕ 710 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል፣ 10 ሚሊዮን 379 ዶላር እና ለኬንያ ከሸጠው ከ314 ሺሕ 931 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል ከ20 ሚሊዮን 470 ሺሕ ዶላር ማግኘቱ ተገልጿል። በተመሳሳይ፣ ተቋሙ ለሱዳን ካቀረበው ከ13 ሺሕ 185 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ከ659 ሺሕ በላይ ዶላር ያገኘ ሲኾን፣ በሱዳኑ ጦርነት ሳቢያ ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ለአገሪቱ ለማቅረብ ካቀደው ኃይል ውስጥ ያቀረበው 15 በመቶውን ብቻ እንደኾነ ተገልጧል። ኢትዮጵያ ውስጥ በዲጂታል መረጃ ማቀነባበር ከተሠማሩ የውጭ ኩባንያዎች በሩብ ዓመቱ ውስጥ ከተሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ደግሞ፣…